
የብርሃን መንገድ - Paperback
Pay over time for orders over $35.00 with
Offers & Perks
Earn 25 points with this purchase
Added to your rewards balance after checkout.
100 points welcome bonus
Create an account and start with extra points.
በዚህ መጽሐፍ የምንመለከተው በዋነኛነት የብርሃንን እንቅስቃሴ እና የወጥ አንጻራዊነት ንድፈ ሐሳብን ነው። በመጀመሪያ ምዕራፍ የመብርሄመግነጢሰት ንድፈ ሐሳቦች እና የማክስዌል ቀመሮች ቀርበዋል ፣ የብርሃንን የመርብርሄመግነጢሳዊ ሞገድ መሆንም እናያለን። በሁለተኛው ምዕራፍ የብርሃን ሥነበሲራዊ ጸባያት (ጽብርቀትን ፣ ስብረትን) ፣ የብርሃን ባሕርይ እና ዕይታ በአጭሩ ቀርበዋል። ምዕራፍ ሦስት የአንጻራዊነት መርኅ እና የማክስዌል የመብርሄመግነጢስ ሞገድ ቀመሮች በጋሊሊዮን መስተዛምድ ከአንድ ወጥ ዋቢ ሥራዓት ወደሌላ ዋቢ ሥርዓት ሲሸጋገሩ የአንጻራዊነትን መርኅ እንደሚጥሱ እንዲሁም የብርሃን ሙግደት በኒውተናዊ ሥነእንቅስቃሴ የተለመደውን የቶሎታ ድመራ ሕግ እንደሚጥስ ያሳየውን የፊዛውን እና የብርሃን ፍጥነት በገዋ (በባዶ ህዋ ፣ ኦና) ውስጥ ከዋቢ ሥርዓት አንጻር የማይለዋወጥ መሆኑን ያሳየውን የማይክልስን እና የሞርሌይን የቤተሙከራ ሥራ ይዟል። ምዕራፍ አራት የአንስታይንን የወጥ አንጻራዊነት ሥነመቸት ንድፈ ሐሳብ ይዟል። በሁሉም ምዕራፎች ውስጥ የተወሰነ የከፍተኛ ርከን ሥነስሌት ዕውቀትን የሚጠይቁ የሒሳብ ሐረጋት እና ቀመሮች አሉ። በዘርፉ ሠፊ ልምድ የሌላቸው አንባቢዎች ጸሓፊው ያሳተማቸውን የቅምሮች እና ቀስቶ ሥፍሮች ሥነስሌት እና የኒውተናዊ ሥነእንቅስቃሴን መጻሕፍት በማንበብ እና በመረዳት እንዲጀምሩ ይበረታታሉ። ልምድ ያለው አንባቢም ቢሆን ሥያሜዎችን ለመልመድ ከተጠቀሱት መጻሕፍት እንዲጀመር ይመከራል።
Free shipping on orders over $75. Standard shipping takes 3-7 business days. Returns accepted within 30 days of purchase.
