Surprise Castle
/Books/Biographies & Autobiographies/History/Military Figures
ጎበና: ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሕይወት (1

ጎበና: ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሕይወት (1 - Hardcover

$54.99
Quantity
01

Pay over time for orders over $35.00 with

Offers & Perks

Earn 54 points with this purchase

Added to your rewards balance after checkout.

100 points welcome bonus

Create an account and start with extra points.

Join now
Availability:In StockContributor:Dechasa AbebePublish date:9/11/2020Pages:324
Languages:AmharicPublisher:Tsehai PublishersISBN-13:9781599072241ISBN-10:1599072246UPC:9781599072241Book Category:Biography & AutobiographyBook Subcategory:MilitarySize:9.00 x 6.00 x 0.88 inchesWeight:0.645Product ID:SC7FFD5S5Z

ጎበና ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሕይወት (1810-1881) - ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ታላቅ ሚና ስለተጫወቱት የፖለቲካ ሰውና የጦር መሪ የራስ ጎበና ዳጪን የሕይወት ታሪክ የያዘ መጽሐፍ ነው።

በአራት ክፍሎችና በዓሥራ አራት ምዕራፎች ተዋቅሮ ክፍል አንድ ከዋናው የታሪክ ዳሰሳና ትንተና በፊት ታሪካዊውን ዳራ ለመተረክ ይሞክራል። ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ጎበና ሊደርስ ከቻለበት የወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ የእውቅና ጣርያ ድረስ ያለፈባቸውን በፈተና የተሞሉ፣ የዚያኑ ያክል በውጤት የታጀቡ የሕይወት ልምዶቹን ለመዳሰስ ጥረት የሚያደርግ ሲሆን፤ ሦስተኛው ከዚሁ ተያያዥ በሆነ መልኩ ጎበና የተጎናጸፈውን እውቅና እንደምን አድርጎ ሀገራዊ ፋይዳ ወደአለው ነገር እንደለወጠ ለማሳየት ይጥራል። ክፍል አራት የጎበና የመጨረሻ ዘመናት ያለ አቻ ወራሽ ሲጠናቀቁ የኦሮሞ ሕዝብ የተጋረጠበትን ከሀገርና ከመንግሥት ባለቤትነት የመንሸራተት ፈተና ለምን እንደተከሠተ ለማመላከት ጥረት ያደርጋል።

በዝርዝር ምዕራፎቹ ስለ ጎበና እስከ አሁን የነበሩትን የተለያዩ እይታዎችና አመለካከቶች፣ ከጎበና መወለድ በፊት በዓሥራ ዘጠነኛው ክፍለዘመን መጀመሪያና በልደቱ ወቅት የጎበና የትውልድ ቦታ በነበረው ሰሜን ሸዋ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ በይበልጥ ደግሞ የኦሮሞና ዐማራ ሕዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብሮች ጎበናን እንዴት እንደቀረጹት፣ የጎበናን ልደት፣ ልጅነትና ወጣትነት እንዲሁም የሎሌነት፣ የአማችነት እና ደጅ አጋፋሪነት በመጨረሻም የሽፍትነት ጊዜውን፣ የግዛት መስፋፋትና የሰፊውን ኢትዮጵያ ሀገር የመመሠረት ውጥንና ከምኒልክ ጋር መተዋወቁን ይገልጻል።

ጎበና የተለያዩ ሹመቶችን ለምሣሌ የደጃዝማችነትና ከዚያም የራስነት ሹመትና ማዕረግ ላይ እንዴት እንደደረሰና በተለይም የጦር አበጋዝነትን ያክል ትልቅ ሃላፊǛ

Languages:AmharicPublisher:Tsehai PublishersISBN-13:9781599072241ISBN-10:1599072246UPC:9781599072241Book Category:Biography & AutobiographyBook Subcategory:MilitarySize:9.00 x 6.00 x 0.88 inchesWeight:0.645Product ID:SC7FFD5S5Z
Abebe, Dechasa: - ዶ/ር ደቻሳ አበበ በጥቅምት 3፣ 1967 ዓ. ም በሰሜን ሸዋ ሳያደብርና ዋዩ ወረዳ ሳክላ አቦ የገጠር ቀበሌ ተወለደ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በደነባ አንደኛ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃውን በእነዋሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል። የመጀመሪያ ድግሪውን ከኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በታሪክ መምህርነት በ1991 ዓ. ም፣ የማስተርስ ድግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ በ1995 ዓ. ም እና ከኢንድራጋንዲ ዩኒቨርሲቲ በሶሽዮሎጂ በ2001 ዓ. ም ያገኘ ሲሆን በታሪክ የትምህርት ዓይነት ደግሞ የዶክትሬት ድግሪ በ2008 ዓ. ም ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል። ዶ/ር ደቻሳ በጋምቤላ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፣ በጅማ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ መምህርነት ያገለገለ ሲሆን አሁን በዚያው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚገኘው የአፍሪካ ጥናትና ምርምር ማዕከል በመምህርነትና በተመራማሪነት በማገልገል ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ በርካታ የጥናት ወረቀቶችን በተለያዩ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚገኙ የምርምር ጆርናሎች ላይ አሳትሟል።
Publisher: Tsehai Publishers

Contributor(s)

Dechasa Abebe

Free shipping on orders over $75. Standard shipping takes 3-7 business days. Eligible items may be returned within 30 days of delivery. Conditions apply.